Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የልብ ንጽሕናን ለሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። ንጹሓንም ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተመረጡ ናቸው። ንጉሥ በከንፈሩ ይገዛል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 22:11
17 Referências Cruzadas  

ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ።


ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።


እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ በሽንገላ ያልማለ።


ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።


አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፥ በሚያሳፍር ላይ ግን ቁጣው ይሆናል።


የጽድቅ ከንፈር የነገሥታት ደስታ ናት፥ በቅን የሚናገር እርሱንም ይወድዱታል።


የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል።


የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፥ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።


ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።


ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios