Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ትእዛዞችን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤ መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ትእዛዝን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚንቅ ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 19:16
25 Referências Cruzadas  

አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ፥ ትእዛዙንም ያደርጉአት ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው።


ትእዛዝን የሚያቃልል በትእዛዝ ተይዞ ይጠፋል፥ ትእዛዝን የሚፈራ ግን በደኅንነት ይኖራል።


ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል።


የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።


ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።


አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።


ራእይ ከሌለ ሕዝብ ከመስመር ይወጣል፥ ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።


ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ክፉ ነገር አይገጥመውም፥ የጠቢብም ልብ ጊዜንና ፍርድን ያውቃል።


ነገር ግን፦ “ድምፄን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ” ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።


የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ስላልተጠነቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅ ኖሮ ነፍሱን ባዳነ ነበር።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


ኢየሱስም፦ “በትክክል መልሰሃል፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ፤” አለው።


እርሱ ግን፦ “በእርግጥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፤” አለ።


“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ።


ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅ፥ በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ፥ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፥ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios