Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ክፉ ነገር ኃጢአተኞችን ያሳድዳቸዋል፥ ጻድቃን ግን መልካሙን ዋጋ ይቀበላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 መጥፎ ዕድል ኀጢአተኛን ይከታተላል፤ ብልጽግና ግን የጻድቃን ዋጋ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኃጢአተኞችን በሄዱበት ስፍራ ሁሉ መከራ ይከተላቸዋል፤ ደጋግ ሰዎች ግን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 13:21
14 Referências Cruzadas  

መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፥ ፍላጎትዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርሷ ልትሰለጥንባት ይገባል።”


የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፥ እንዳይነሡም ወደ እሳትና ወደ አዘቅት ይጣሉ።


በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት፥ በጌታ የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል።


እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።


እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥ ይልቁንስ ክፉዎችና ዓመፀኞችስ እንዴት ይሆኑ!


ትእዛዝን የሚያቃልል በትእዛዝ ተይዞ ይጠፋል፥ ትእዛዝን የሚፈራ ግን በደኅንነት ይኖራል።


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፤ ደግሞም ይነሣል፥ ክፉዎችን ግን መጥፎ ነገር ሲገጥማቸው ይወድቃሉ።


በዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፥ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ጉዳት ይወድቅብሻል ልታስወግጂውም አትችይም፤ የማታውቂያትም ጉስቁልና ድንገት ትመጣብሻለች።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በክፋት ላይ ክፋት እነሆ፥ ይመጣል።


እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል፤ ኃጢአታችሁም በእውነት እንደሚያገኛችሁ እወቁ።


አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios