Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው ሬሳን በመንካት ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ እንዲህም ሆኖ እንኳ ለጌታ የፋሲካን በዓል ያክብር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከእናንተ ወይም ከዘሮቻችሁ ማንኛውም ሰው በሬሳ ምክንያት ቢረክስ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ማክበር ይችላል፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእናንተም ሆነ ከዘራችሁ ሰዎች በድን በመንካት ቢረክሱ ወይም ወደ ሩቅ አገር ለመሄድ በጒዞ ላይ ቢሆኑና የፋሲካን በዓል ለማክበር ቢፈልጉ፥

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ወይም ከት​ው​ል​ዶ​ቻ​ችሁ ዘንድ ማን​ኛ​ውም ሰው በሰ​ው​ነቱ ቢረ​ክስ፥ ወይም ሩቅ መን​ገድ ቢሄድ፥ ወይም በተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​በት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን ያድ​ርግ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 9:10
15 Referências Cruzadas  

በሁለተኛውም ወር የቂጣውን በዓል ሊያከብር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆነ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ።


እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ብዙ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ “ቸሩ ጌታ ሆይ! ሁሉንም ሰው ይቅር በል፤


ንጉሡና አለቆቹ የኢየሩሳሌምም ጉባኤ ሁሉ በሁለተኛው ወር ፋሲካውን ለማክበር ተመካክረው ነበር።


በዓሉንም በሁለተኛው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ ያክብሩ፤ እርሾ ካልገባበት ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


መባህን እዚያው በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፤ አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ ከዚያ በኋላ መጥተህ መባህን አቅርብ።


የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።


ሰው ግን ራሱን ይመርምር፤ እንዲሁም ከኅብስቱ ይብላ፤ ከጽዋውም ይጠጣ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios