Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 8:26
10 Referências Cruzadas  

ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”


በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።


በመቅደሴ ውስጥ ሥርዓቴን ጠባቂዎች ለራሳችሁ አስቀመጣችሁ እንጂ የተቀደሰውን ነገሬን ሥርዓት አልጠበቃችሁም።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”


ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ግዴታዎች ይፈጽሙ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።


የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም የመቅደሱን ግዴታ በሚፈጽሙት ላይ ተቆጣጣሪ ይሆናል።


ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከኀምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”


ዕድሜአቸውም ኀምሳ ዓመት ሲሞላ አገልግሎታቸውን ይተዋሉ፥ ከዚያም በኋላ አይሠሩም፤


እድገትህ በሁሉ ሰው ፊት እንዲገለጥ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ በሥራ ላይ አውል፤ ለእነርሱም ራስህን ሙሉ በሙሉ በመስጠት ትጋ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios