Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 4:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ይህ ከቀዓት ጐሣዎች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው። ሙሴና አሮን፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ቈጠሯቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የቀዓት ቤተሰቦች ሁሉ እነዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የሚ​ገ​ቡት ሁሉ፥ የቀ​ዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 4:37
7 Referências Cruzadas  

ጌታም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰጣቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።


ሙሴም እንደ ጌታ ቃል፥ እንደ ታዘዘው ቈጠራቸው።


በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።


በየወገኖቻቸውም ከእነርሱ የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ኀምሳ ነበሩ።


በየወገኖቻቸውም በየአባቶቻቸውም ቤቶች የተቈጠሩት የጌድሶን ልጆች፥


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራትና ዕቃውን ለመሸከም የገቡት ሁሉ፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥


እንደ ጌታ ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ ተደለደሉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios