Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 35:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እስራኤላውያን ከወረሷት ምድር ላይ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች እያንዳንዱ ነገድ እንዳለው ድርሻ መጠን ይሆናል። ብዙ ካለው ነገድ ላይ ብዙ ከተሞች እንዲሁም ጥቂት ካለው ነገድ ላይ ጥቂት ከተሞችን ውሰዱ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከእስራኤላውያን ይዞታ እንደየርስታቸው መጠን፥ ብዛት ካላቸው ነገዶች ብዙ ከተሞችን፥ አነስ ካሉ ነገዶች ጥቂት ከተሞችን ወስደህ ለሌዋውያን ስጥ።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 35:8
11 Referências Cruzadas  

ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።


የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


በዖሜርም በሰፈሩት ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም ጥቂት የሰበሰበውም አላነሰውም፤ የሰበሰቡት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ነው።


ነገር ግን ለሌዋውያን ርስታቸው በሆኑት በሌዋውያን ከተሞች ውስጥ ያሉትን ቤቶች ለዘለዓለም የመቤዠት መብት አላቸው።


በየወገናቸው ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል።


ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios