Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማርቆስ 2:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለምን ያደርጋሉ?” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ፈሪሳውያንም፣ “እነሆ፤ በሰንበት ቀን ለምን ያልተፈቀደውን ነገር ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለምን ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ?” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ፈሪሳውያንም፦ እነሆ፥ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ? አሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ማርቆስ 2:24
18 Referências Cruzadas  

ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህ፥ ሴት ልጅህ፥ ወንድ ሠራተኛህ፥ ሴት ሠራተኛህ፥ ከብትህ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ ሁሉ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤


ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።


ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰንበቴን ለሚጠብቁ፥ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ለሚመርጡ፥ ቃል ኪዳኔንም ለሚይዙ ጃንደረቦች፥


ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥


ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥


ፈሪሳውያን ይህንን አይተው “እይ! ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ሊደረግ የማይገባውን ያደርጋሉ፤” አሉት።


ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድነው?” አሉ።


እርሱም “ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥


ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል፤” ብለው አሰቡ።


በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ እንዴት እንደተቋቋመ አስቡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios