Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 11:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 እናንተ ሕግ አዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችኋልና፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ የሚገቡትንም ከለከላችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 “እናንተ ሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ነጥቃችሁ ወስዳችኋልና፤ እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ የሚገቡትንም ከልክላችኋል።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 “እናንተ የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! የዕውቀት በር መክፈቻ የሆነውን የእውነት ቊልፍ ይዛችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 11:52
10 Referências Cruzadas  

የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


እርሱም ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ ጻፎችና ፈሪሳውያን እርሱን እጅግ በመቃወም ስለ ብዙ ነገሮች የትንኮሳን ጥያቄ ይጠይቁት ጀመር፤


ሰሙትም፤ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፤ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios