Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከመንጋውም እንከን የሌለበትን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አውራ በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያምጣ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለበደሉም ማስተስረያ ምንም ነውር የሌለበት አንድ ተባዕት በግ ወይም በታወቀው ተመን የተተመነውን ገንዘብ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ።።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 6:6
8 Referências Cruzadas  

ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።


በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥


ወደ ሰሜን የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፤ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል እንዲያገለግሉት ወደ ጌታ የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው።”


ካህኑም አንዱን ተባት ጠቦት ይወስዳል፤ እርሱንም ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ጎን ለጎንም ዘይቱ ያለበትን የሎግ መስፈሪያውን፤ እነርሱንም ስለ መወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል።


“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።


ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።


“እርሱም ጠቦትን ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት ሌላውን ደግሞ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለጌታ ያመጣል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios