Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 27:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርሱም ሊቤዠው ቢወድድ ግን በተገመተው ላይ አምስት እጅ ይጨምር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ባለቤቱ እንስሳውን መዋጀት ከፈለገ ግን፣ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ባለቤቱም እንስሳውን መልሶ ለመግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ በመቶ ኻያ እጅ ይጨምር።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ግን ከግ​ምቱ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ይቤዠውም ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ በላይ አምስተኛ ይጨምር።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 27:13
9 Referências Cruzadas  

ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ነገር ቢበላ በፊት በነበረው ላይ አምስት እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ነገር ለካህኑ ይስጥ።


መልካሙን በክፉ ወይም ክፉውን በመልካም ቢሆንም እንኳ እርሱን በሌላ አትተካ ወይንም አትለውጥ፤ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ።


ካህኑም መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይሁን።


“ለጌታም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ሰው ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይጸናል።


የቀደሰውም ሰው ቤቱን ሊቤዠው ቢወድድ በገመትከው የገንዘብ መጠን ላይ አምስት እጅ ይጨምራል፤ ቤቱም ለእርሱ ይሆናል።


እርሻውንም የቀደሰ ሰው ሊቤዠው ቢወድድ፥ በገመትከው የገንዘብ መጠን ላይ አምስት እጅ ይጨምራል፤ ከዚያም ለእርሱ ይጸናለታል።


የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምትህ መጠን ይቤዠዋል፤ በእርሱም ዋጋ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምትህ ይሸጣል።


በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኃጢአት ዕዳ ይከፍላል፥ በሚከፍለውም ዕዳ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፥ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios