Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 25:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ከወገንህ አንዱ ደኽይቶ ርስቱን ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ መጥቶ ወገኑ የሸጠውን ይዋጅለት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አንድ እስራኤላዊ ድኻ ሆኖ መሬቱን ለመሸጥ ቢገደድ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ሊዋጅለት ይገባዋል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 25:25
14 Referências Cruzadas  

በርስት በያዛችሁት ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ ታደርጋላችሁ።


የሚቤዠውም ሰው ባይኖረው፥ እርሱም ቢበለጥግ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥


“በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም በአንተ ዘንድ ለተቀመጠው እንግዳ ወይም ለመጻተኛው የቤተሰብ አባላት ቢሸጥ፥


ከርስቱ እርሻ ያልሆነውን የገዛውን እርሻ ለጌታ ቢቀድስ፥


የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ናዖሚም ምራትዋን፦ “በሕያዋን እና በሙታን ላይ ቸርነቱ የማያልቅበት ጌታ የተባረከ ይሁን” አለቻት። ናዖሚም ደግሞ፦ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው” አለቻት።


የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፥ ነገር ግን ከእኔ ይልቅ ቅርብ የሆነ ሌላ ዘመድ አለ፤


አሁንም ስትቃርሚ አብረውሽ የነበሩት ሴቶች የሚያገለግሉት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።


እርሱም፦ “ማን ነሽ?” አለ። እርሷም፦ “እኔ ባርያህ ሩት ነኝ፥ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባርያህ ላይ ጣል አለችው።”


ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን፦ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ናዖሚ የወንድማችንን ኤሊሜሌክን መሬት መሸጥ ትፈልጋልች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios