Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 13:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ያየዋል፤ በቆዳውም ላይ ቢስፋፋ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በሰባተኛው ቀን ካህኑ ይመርምረው፤ በሽታውም በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ቢያገኘው፣ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ እንደገና ይመርምረው፤ ቊስሉ ተስፋፍቶ ከተገኘ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ስለዚህም ያ ሰው የረከሰ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ያየ​ዋል፤ በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ያየዋል፤ በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 13:27
6 Referências Cruzadas  

ማናቸውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሰውነቱ ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ቢሆን፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


ነገር ግን ካህኑ ቢያየው፥ በቋቁቻውም ላይ ነጭ ጠጉር ባይኖር፥ ከቆዳውም በታች ባይዘልቅ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል።


ቋቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የቃጠሎው እባጭ ነው፤ የቃጠሎውም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።


ከነጻ በኋላ ግን ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፥


ስለ መንጻቱ በካህኑ ዘንድ ከታየ በኋላ እከኩ በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፥ እንደገና ሊታይ ወደ ካህኑ ይቀርባል።


ካህኑም በሰባተኛው ቀን ተመልሶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግድግዳ ላይ ቢሰፋ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios