Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የወይራ ዛፍም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እግዚአብሔርና ሰዎች የሚከበሩበትን ዘይቴን መስጠት ልተውን?” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “የወይራ ዛፍም፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ እግዚአብሔርና ሰዎች የሚከበሩበትን ዘይቴን መስጠት ልተውን?’ አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የወይራ ዛፍም ‘ለአማልክትና ለሰዎች ጠቃሚ የሆነውን ዘይቴን መስጠት ትቼ በዛፎች ላይ ልንገሥን?’ አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ወይ​ራዋ ግን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን የሚ​ያ​ከ​ብ​ር​በ​ትን ቅባ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ ለመ​ን​ገሥ ልሂ​ድን? አለ​ቻ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ወይራው ግን፦ እግዚአብሔርና ሰዎች በእኔ የሚከበሩበትን ቅባቴን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 9:9
14 Referências Cruzadas  

ጌታም ሰይጣንን፦ “ከወዴት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁአት፥ በእርሷም ተመላለስሁ” ብሎ ለጌታ መለሰ።


ጌታም ሰይጣንን፦ “ከወዴት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም፦ “በምድር ላይ ዞርሁ፥ በእርሷም ተመላለስሁ” ብሎ ለጌታ መለሰ።


ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥ እህልም የሰውን ጉልበት ያጠነክራል።


በዚያ ጊዜ ለታማኞችህ በራእይ ተናገርህ፥ እንዲህም አልህ፦ ረድኤቴን በኃያል ላይ አኖርሁ፥ ከሕዝቤ የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ።


ያልቦካ ቂጣ፥ በዘይት የተለወሰ ያልቦካ እንጎቻ፥ በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ፥ ከመልካም ስንዴ አዘጋጅ።


የቅባትን ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባዋለህም።


መብራት የሚያበሩበትን መቅረዝና ዕቃውን፥ ቀንዲሉን፥ የመብራቱን ዘይት፤


“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።


እናንተ ግን ከቅዱሱ፥ ቅባት አላችሁ፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።


ቀጥሎም ዛፎቹ በለስን፥ “መጥተህ ንጉሣችን ሁን” አሉት።


ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች የሚያነግሡትን ለመቀባት ወጡ፤ ወይራንም፥ “አንተ ንጉሣችን ሁን” አሉት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios