Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 19:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ እኛ ባሮችህ ለእኔም ሆነ ለገረድህ፥ አብሮን ላለውም ወጣት እንጀራና የወይን ጠጅ ይዘናል፤ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ እኛ ባሮችህ ለእኔም ሆነ ለገረድህ፣ ዐብሮን ላለውም ወጣት እንጀራና የወይን ጠጅ ይዘናል፤ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኛ ግን ለአህዮቻችን ገፈራና ገለባ፥ ለቊባቴና ለእኔ እንዲሁም ለአገልጋዬ እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ የሚያስፈልገንን ሁሉ ይዘናል፤ ምንም ያጣነው ነገር የለም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ችን ገለ​ባና ገፈራ አለን፤ ለእ​ኔና ለገ​ረ​ድህ ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ጋር ላለው ብላ​ቴና እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አለን፤ ከሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገን ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ጣ​ንም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፥ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው አሽከር እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፥ አንዳችም አላጣንም አለው።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 19:19
6 Referências Cruzadas  

በእኛ ዘንድ ገለባና ገፈራ የሚበቃ ያህል አለ፥ ለማደሪያም ደግሞ ስፍራ አለን።”


“እንደ ቀድሞው ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ሄደው ገለባ ይሰብስቡ።


እርሱም ወደ ውስጥ ጠርቶ እንድግድነት ተቀበላቸው። በነገውም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ወጣ፤ በኢዮጴም ከነበሩት ወንድሞች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ።


እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።


ወደ የቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፥ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ የቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው።


ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኛ የመጣነው ከይሁዳ ቤተልሔም ርቆ ከሚገኘው ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር ነው፤ ከይሁዳ ቤተልሔም ነበርሁ፤ አሁን ወደ ጌታ ቤት እሄዳለሁ፤ ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ሰው አላገኘሁም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios