Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 17:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ ብሩን ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም ከላዩ ሁለት መቶ ጥሬ ብር ወስዳ ለብር አንጥረኛ ሰጠች፤ አንጥረኛውም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት አደረገው፤ ምስሎቹም በሚካ ቤት ተቀመጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ብሩን ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም ከላዩ ሁለት መቶ ጥሬ ብር ወስዳ ለብር አንጥረኛ ሰጠች፤ አንጥረኛውም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት አደረገው፤ ምስሎቹም በሚካ ቤት ተቀመጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ልጁም ብሩን ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም ከላዩ ሁለት መቶ ብር አንሥታ እንጨት ጠርቦ በብሩ በመለበጥ ጣዖት ለሚሠራላት የብር አንጥረኛ ሰጠችው፤ ጣዖቱም በሚካ ቤት ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለእ​ና​ቱም ገን​ዘ​ቡን መለ​ሰ​ላት እና​ቱም ብሩን ወስዳ ከእ​ርሱ ሁለ​ቱን መቶ ብር ለአ​ን​ጥ​ረኛ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አደ​ረ​ገው። በሚ​ካም ቤት አስ​ቀ​መ​ጡት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወስዳ ለአንጥረኛ ሰጠችው፥ እርሱም የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አደረገው። ያም በሚካ ቤት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 17:4
9 Referências Cruzadas  

በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።


ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል።


ሠሪው የቀረጸውና ቀልጦ የተሠራ ምስል የውሸት አስተማሪ ነውና፤ ዲዳ ጣዖትን በመሥራት ሠሪው በሠራው ይታመናልና፤ የተቀረጸ ምስል ምን ይጠቅማል?


“‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።


ሚካ የተባለው ይህ ሰው የአምልኮ ስፍራ ነበረው፤ አንድ ኤፉድና ተራፊም ሠርቶ ከልጆቹ አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ።


ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፥ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን አምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፥ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios