Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት፣ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእስራኤላውያን ፊት ቀድመው ተሻገሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከሮቤልና ከጋድ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለጦርነት የተዘጋጁት ሰዎች ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት ከሕዝቡ ግንባር ቀደም ሆነው ተሻገሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 4:12
9 Referências Cruzadas  

ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ዞረው በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መንገድ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ምድር ለጦርነት ተሰልፈው ወጡ።


“የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥


እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንድሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ።


በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።


በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፥ ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፥ የጌታንም ጽድቅ፥ ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።”


ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፤ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥


ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ፥ ሕዝቡ እያዩ የጌታ ታቦትና ካህናቱ ተሻገሩ።


አርባ ሺህ ያህል ሰዎች መሣርያ ታጥቀው ለጦርነት በጌታ ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios