Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከእነርሱም ብዙዎች “ጋኔን አለበት፤ አብዶአልም፤ ለምንስ ትሰሙታላችሁ?” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ብዙዎቹም፣ “ጋኔን ያደረበት እብድ ነው፤ ለምን ትሰሙታላችሁ?” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከእነርሱም ብዙዎቹ፥ “እርሱ ጋኔን አለበት፤ አብዶአል፤ ስለምን ትሰሙታላችሁ?” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከእነርሱም ብዙዎች፦ “ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ?” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 10:20
15 Referências Cruzadas  

በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?


‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።


ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?


ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት።


ፈሪሳውያን ግን “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል” አሉ።


ዘመዶቹም “አእምሮውን ስቷል” ሲባል ሰምተው ሊይዙት መጡ።


ሕዝቡ መለሱና “ጋኔን አለብህ፤ ማን ሊገድልህ ይፈልጋል?” አሉት።


አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።


እንዲህም ብሎ ስለ ራሱ ሲመልስ ፊስጦስ በታላቅ ድምፅ “ጳውሎስ ሆይ! አብድሃል እኮ፤ ብዙ ትምህርትህ ወደ እብደት ያዞርሃል፤” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios