Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ድብ የሚባለውን እና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ሠርቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱ የድብና የኦሪዮን፣ የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ድብ፥ ኦሪዮንና፥ ፕልያዲስ የተባሉትን ከዋክብት፥ እንዲሁም በደቡብ በኩል ያሉትን የከዋክብት ክምችቶች በሰማይ ላይ ያኖራቸው እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ድብ የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከ​ብና ኦሪ​ዮን የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከብ፥ የአ​ጥ​ቢያ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም፥ በአ​ዜ​ብም በኩል ያሉ​ትን የከ​ዋ​ክ​ብት ማደ​ሪ​ያ​ዎች ፈጥ​ሮ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኵል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ሠርቶአል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 9:9
8 Referências Cruzadas  

እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።


ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።


ተራሮችን ከላይ የምታጠጣቸው፥ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች።


እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሠረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥


የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።


ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።


ከዚያም እየተዛወርን ወደ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ መጣን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios