Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣ የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሱ የሚያደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች መርምረን ልናስተውል አንችልም፤ እርሱም የሚፈጽማቸውን ተአምራት ልንቈጥራቸው አንችልም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ታላ​ቁ​ንና የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ነገር፥ እን​ዲ​ሁም የከ​በ​ረ​ው​ንና እጅግ መል​ካም የሆ​ነ​ውን የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 9:10
14 Referências Cruzadas  

ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥ በኃይል ታላቅ ነው፥ በፍርድና በጽድቅም ሃብታም ነው፤ አይጨቁንምም።


እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።


ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥ ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።


መዘርዘር ከምችለው በላይ ቢሆንም፥ አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።


ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለማዊነትን በልቡ ሰጠው።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው።


እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios