Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 8:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥ የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤ በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሥሮቹም በድንጋይ ካብ ላይ ይጠመጠማሉ፤ በየቋጥኙም ላይ ይጣበቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በድ​ን​ጋይ ክምር ላይ ያድ​ራል፤ በድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም መካ​ከል ይኖ​ራል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፥ የድንጋዩቹን ቦታ ይመለከታል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 8:17
9 Referências Cruzadas  

ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል።


ሥሬ በውኃ ላይ ተዘርግተው፥ ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድር ነበር፤


ከፀሐይም ትኩሳት በፊት እርጥብ ነው፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል።


ከቦታው ቢጠፋ፦ አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።


ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፥ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፥ እነርሱም ደረቁ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው።


ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።


በማግስቱ ጠዋት በመንገድ ሲያልፉ፥ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ።


እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios