Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 41:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሲያስነጥስ ብልጭታ ያወጣል፥ ዐይኖቹም እንደ ንጋት ወገግታ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሊቀሰቅሰው የሚደፍር የለም፤ ማን ፊቱ ሊቆም ይችላል?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በእርሱ ላይ አደጋ መጣል ይህን ያኽል አደገኛ ከሆነ፥ ታዲያ፥ እኔን ለመቃወም የሚደፍር ማነው?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከአፉ የሚ​ቃ​ጠል መብ​ራት ይወ​ጣል የእ​ሳ​ትም ፍን​ጣሪ ይረ​ጫል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንጥሽታው ብልጭታ ያወጣል፥ ዓይኖቹም እንደ ወገግታ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 41:10
13 Referências Cruzadas  

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?


ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት።


የንጋቱ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፥


እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጉዳለህን?


እርስ በርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው፥ እስከማይለያዩም ድረስ ተያይዘዋል።


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


“ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ተሰናክለህ ከወደቅህ፥ በዮርዳኖስ ዱር እንዴት ታደርጋለህ?


እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርረዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?


እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርራቸዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?


እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚባርክህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን።”


ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios