Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 38:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37-38 የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው? ትቢያ በተበጠበጠ ጊዜ፥ ጓሎቹም በተጣበቁ ጊዜ፥ የሰማይን ደመና ለዝናብ ሊያዘነብል የሚችል ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ትቢያ ሲጠጥር፣ ጓሎችም እርስ በርስ ሲጣበቁ፣

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37-38 በጥበቡ ደመናን ለመቊጠር የሚችል ማነው? የተሰበሰበው ዐፈር ርሶ ጭቃ እንዲሆን ከማከማቻው ከሰማይ ውሃ ወደታች ለማፍሰስ የሚችል ማነው?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የሰ​ማ​ይን ደመና በጥ​በቡ ሊቈ​ጥር የሚ​ችል ማን ነው? ሰማ​ይ​ንም ወደ ምድር ያዘ​ነ​በለ ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37-38 የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው? ትቢያ በተበጠበጠ ጊዜ፥ ጓሎቹም በተጣበቁ ጊዜ፥ የሰማይን ረዋት ሊያዘነብል የሚችል ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 38:37
8 Referências Cruzadas  

ወደ ሜዳም አወጣውና፦ “ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ቁጠር” አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።


ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥


እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥


በእኔና በእናንተ፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ፍጥረት መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ውኃም ዳግመኛ ፍጥረትን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የውኃ ሙላት አይመጣም።


የውኆች ሙላት ይሸፍንህ ዘንድ። ቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን?


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios