Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤ እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፤ በአካሄዱም መጠን የሚገባውን ያደርግለታል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመ​ል​ስ​ለ​ታል፥ ሰው​ንም እንደ መን​ገዱ ያገ​ኘ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለሰው ሥራውን ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 34:11
18 Referências Cruzadas  

ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ይሰማዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም የጽድቁን ዋጋ ይመልስለታል።


ሥራቸውን ያውቃል፥ በሌሊት ይገለባብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቃሉ።


እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፥ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥


ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ።


የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል።


እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?


እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቁጣን ለባላጋራዎቹ፥ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፤ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።


“እኔ ጌታ ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ልብን እመረምራለሁ ኩላሊትንም እፈትናለሁ።”


በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ዐይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።


በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፍንም ቢወስድ፥ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ እነዚህን ርኩሰቶች ሁሉ አድርጎአልና በእርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፥ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።


ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios