Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “ደግሞ በአልጋ ላይ በስቃይ ይገሥጸዋል፥ አጥንቱም ሁሉ ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ደግሞም ሰው ታምሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣ በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ወይም እንደገና ሰው በአጥንቱ ውስጥ በማያቋርጥ በሽታ በአልጋ ቊራኛነት እንዲገሠጽ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ደግሞ በአ​ልጋ ላይ በደዌ ይገ​ሥ​ጸ​ዋል፥ አጥ​ን​ቱም ሁሉ ይን​ቋ​ቋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደግሞ በአልጋ ላይ በደዌ ይገሥጸዋል፥ አጥንቱንም ሁሉ ያደነዝዛል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 33:19
18 Referências Cruzadas  

አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።


በነገሠም በሠላሳ ዘጠኝኛው ዓመት አሳ እግሩን ታመመ፤ ደዌውም ጸናበት፤ ነገር ግን በታመመ ጊዜ ባለ መድኃኒቶችን እንጂ ጌታን አልፈለገም።


አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥ ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።”


የግፈኛውን መንጋጋ እሰብር፥ የነጠቀውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጥል ነበር።


የሌሊቱ ስቃይ እስከ አጥንቶቼ ድረስ ይዘልቃል፥ ሁለመናዬንም ስለሚበላኝ ጅማቶቼ አያርፉም።


በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ። ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥ እስኪ ነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ።


በፊት ስቼ ከመንገድህ ርቄ ነበር፥ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።


ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።


ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።


ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።


የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና።


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።


ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።


እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios