Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥ መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱ እኮ ጊዜአቸው ሳይደርስ ተቀሥፈዋል፤ በጐርፍም ተጠራርገው ሥር መሠረታቸው ጠፍቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጊዜ​ያ​ቸው ሳይ​ደ​ርስ ተነ​ጠቁ፤ መሠ​ረ​ታ​ቸ​ውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥ መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 22:16
19 Referências Cruzadas  

ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥


ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።


ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም።


ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፥ በሰላምም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።”


በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደሚወስደው ትቢያ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?”


“እነርሱ በውኃ ላይ ተንሳፈው ያልፋሉ፥ ድርሻቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፥ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይመለሱም።


በሕፃንነታቸው ሳሉ ይሞታሉ፥ ሕይወታቸውም በሰዶማውያን መካከል ይጠፋል።


ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፥ መሠረታቸው በትቢያ ውስጥ የሆነ፥ ከብል በፊት የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ?


በመንገዴ ጉልበቴ ዛለ፦ ዘመኔም አጠረ።


ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።


ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።


ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች።


እጅግ ክፉ አትሁን፥ አላዋቂም አትሁን፥ ጊዜህ ሳይደርስ ለምን ትሞታለህ?


እነሆ፥ በጌታ ዘንድ ኃያልና ብርቱ የሆነ አለ። እንደ በረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እንደሚያጥለቀልቅም ጎርፍ፥ በጠነከረ እጅ ወደ ምድር ይጥላታል።


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ፥ ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ፥ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios