Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ፤ ስለዚህም ማጕረምረሜን ያለ ገደብ እለቅቃለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “መኖር ሰልችቶኛል፤ የማሳልፈውን መራራ ሕይወት በግልጽ አሰማለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት፥ የኀዘን እንጕርጕሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 10:1
21 Referências Cruzadas  

ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!


በእውነትም የሳትሁ እንደሆነ፥ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።


በራብ ጊዜ ከሞት፥ በሰልፍም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።


ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን?


“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።


ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።


ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፥ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።


ግን ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፥ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።


እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ምክንያት ሆነ፤ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጉድጓድ አዳንካት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ።


አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


እንዲህስ ከምታደርግብኝ፥ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፥ በእኔ ላይ የሚሆነውን መከራ እንዳላይ፥ እባክህ፥ ፈጽሞ ግደለኝ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios