Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 48:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል?፥ ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በዓሮዔር የምትኖሩ ሁሉ፥ በመንገድ ዳር ቆማችሁ ተጠባበቁ፤ የሚሸሹትን ወንዶችና የሚያመልጡትን ሴቶች ሁሉ በመጠየቅ፥ የሆነውን ነገር ሁሉ ዕወቁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ሮ​ዔር የም​ት​ኖሪ ሆይ! በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ቆመሽ ተመ​ል​ከቺ፤ የሸ​ሸ​ው​ንና ያመ​ለ​ጠ​ውን፦ ምን ሆኖ​አል? ብለሽ ጠይ​ቂው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፥ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፥ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 48:19
10 Referências Cruzadas  

ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፥ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ያእዜር ሄዱ፤


እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዮኤል ልጅ የሽማዕ ልጅ የዖዛዝ ልጅ ቤላ ነበር፤


የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥ አሮዔርን ሠሩ፤


በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥


እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረበት በዚያን ጊዜ ስለምን አልወሰዳችኋቸውም?


ሰውየውም ዔሊን፥ “ከጦሩ ሜዳ ገና አሁን መምጣቴ ነው፤ ከጦርነቱ አምልጬ የወጣሁትም ዛሬውኑ ነው” ብሎ ነገረው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፤ ታዲያ እንዴት ሆነ?” ሲል ጠየቀ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios