Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 36:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ በጌታ ቤት የጌታን ቃላት ከመጽሐፉ እንዲያነብ ያዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ አደረገ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የኔርያ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ የነገረውን ሁሉ አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔርን ቃል ከብራናው አነበበ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህም ባሮክ ልክ እኔ እንደ ነገርኩት በቤተ መቅደስ የእግዚአብሔርን ቃል አነበበ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የኔ​ር​ዩም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ጽ​ሐፉ አነ​በበ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 36:8
9 Referências Cruzadas  

በውኃው በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶች፥ ሴቶች፥ የሚያስተውሉም ባሉበት፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ በጽሞና ያደምጥ ነበር።


አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ በእነርሱ ፊት እንዳላስፈራህ አትፍራቸው።


የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ የፈረሙት ምስክሮች፥ በእስርም ቤት አደባባይ የተቀመጡት አይሁድ ሁሉ እያዩ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።


ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም ኤርምያስ እየነገረው ጌታ ለእርሱ የተናገረውን ቃላት ሁሉ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።


አንተ ግን ሂድ፥ እየነገርሁህም የጻፍኸውን የጌታን ቃላት በጾም ቀን በጌታ ቤት በሕዝቡ ጆሮ ከክርታሱ አንብብ፤ እንዲሁም ደግሞ ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “ሊከተለኝ የሚወድ ራሱን ይካድ፥ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፥ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና፥ አብሮአችሁ ያለ ሥጋት እንዲቀመጥ አድርጉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios