Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 27:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱን አትስሙ፤ ለባቢሎን ንጉሥ አገልግሉ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ለምን ባድማ ትሆናለች?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ባለመታዘዛችሁስ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ብትገዙለት በሕይወት ትኖራላችሁ፤ ይህችስ ከተማ ስለምን የፍርስራሽ ክምር ሆና ትቀራለች?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ር​ሱን አት​ስሙ፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ፤ ይህ​ችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆ​ና​ለች?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነርሱም አትስሙ፥ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች?

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 27:17
5 Referências Cruzadas  

ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች በእርግጥ ብትወጣ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ።


ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”


የምትፈሩትን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩት፤ እናንተን ለማዳን ከእጁም ለመታደግ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እርሱን አትፍሩ፥ ይላል ጌታ።


ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios