Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 22:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ እንዲህ አለ፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት ውረድ፤ ይህንም መልእክት በዚያ እንዲህ ብለህ ተናገር፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1-2 እግዚአብሔር የዳዊት ዘር ወደ ሆነው ወደ ይሁዳ ቤተ መንግሥት እንድወርድና በዚያም ለንጉሡ፥ ለመኳንንቱና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እኔ የምነግራቸውን ቃል እንዲያዳምጡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለኝ፦

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ይህን ቃል ተና​ገር፥ እን​ዲ​ህም በል፦

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 22:1
15 Referências Cruzadas  

ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ።


ጌታም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ግን አልሰሙትም።


“የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ።


እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በጫካዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”


እንዲህም በል፦ በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! አንተና ባርያዎችህ፥ በእነዚህም በሮች የሚገባው ሕዝብህ፥ የጌታን ቃል ስሙ።


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ በእሳትም ያቃጥላታል፤


ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።


ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ዳግመኛ ትንቢት አትናገር።”


ዮሐንስ ሄሮድስን፥ “የወንድምህን ሚስት ታገባት ዘንድ ሕግ ይከለክልሃል” ይለው ነበርና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios