Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ ‘እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል ጌታ፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታስገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ነገር ግን በጥንቃቄ ብትታዘዙኝ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡ፣ የሰንበትንም ቀን ምንም ሳትሠሩ ብትቀድሱት፣

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እኔን ፈጽሞ ብት​ሰሙ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን በዚ​ህች ከተማ በሮች ሸክም ባታ​ገቡ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን ብት​ቀ​ድሱ፥ ሥራ​ንም ሁሉ ባት​ሠ​ሩ​ባት፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 17:24
11 Referências Cruzadas  

እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


“እንድትቀድሰው የሰንበትን ቀን አስታውስ።


በከብት የሚቀመጡትን፥ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ፈረሰኞች፥ በአህዮች የሚቀመጡትንና በግመሎች የሚቀመጡትን ባየ ጊዜ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ።


እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ።


በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።


“ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥


“አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios