Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 53:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሟሟቱን ከክፉዎችም ጋር፥ መቃብሩን ከባለጠጎችም ጋር አደረጉ፤ ግፍ ግን አላደረገም ነበር፤ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በአፉም ሳያታልል፣ ዐመፃም ሳያደርግ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋራ ሆነ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ምንም ዐመፅ ሳይፈጽም፥ በአንደበቱም ሐሰት ሳይገኝበት፥ በሞቱ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ተቈጠረ፤ በባለጸጋም መቃብር ተቀበረ።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ክፉ​ዎ​ች​ንም ስለ መቃ​ብሩ፥ ባለ​ጸ​ጎ​ች​ንም ስለ ሞቱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ምና፥ ከአ​ፉም ሐሰት አል​ተ​ገ​ኘ​በ​ት​ምና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፥ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 53:9
11 Referências Cruzadas  

ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤


እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።


እኛ ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


እርሱ ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም፤


ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios