Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 39:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ “የተናገርኸው የጌታ ቃል መልካም ነው” አለው። ደግሞም፦ “በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” አለው፤ “በዘመኔ ሰላምና ጸጥታ ከኖረ ዘንድ” ብሎ ዐስቦ ነበርና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ንጉሥ ሕዝቅያስ በተለይ በእርሱ ዘመን፥ በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለ ስለ ተረዳ “ከእግዚአብሔር ተልከህ የነገርከኝ ቃል መልካም ነው” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እርሱ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መል​ካም ነው፤ ነገር ግን፦ በዘ​መኔ ሰላ​ምና ጽድቅ ይሁን” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው አለው። ደግሞም፦ በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 39:8
12 Referências Cruzadas  

ነገር ግን እርሱ፥ ‘ባንተ አልተደሰትሁም’ የሚል ከሆነ፥ እነሆኝ፥ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግብኝ።”


ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኩራት ራሱን አዋረደ፥ የጌታም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።


እነሆ፥ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራና በሚኖሩባትም ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ይህንም ለንጉሡ አወሩለት።


እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”


ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።


ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጉረመርም ስለ ምንድነው?


ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


እንግዲህ የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፦ እርስ በእርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም መግቢያዎች ሐቀኛና ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ!


እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።


ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios