Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 37:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 “ስለዚህም ጌታ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም አይደለድልባትም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 “ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ “ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤ ፍላጻም አይወረውርባትም፤ ጋሻ አንግቦ አይቀርብም፤ በዐፈርም ቍልል አይከብባትም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 “ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሥ የተናገረውም ቃል ይህ ነው፤ ‘ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በዐፈር ቊልልም አትከበብም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ወደ​ዚች ከተማ አይ​መ​ጣም፤ ፍላ​ጻ​ንም አይ​ወ​ረ​ው​ር​ባ​ትም፤ በጋ​ሻም አይ​መ​ጣ​ባ​ትም፥ አያ​ጥ​ራ​ት​ምም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 37:33
11 Referências Cruzadas  

እንደ ባሕር ሞገድ ለሚተም የብዙ ሕዝቦች ጩኸት፥ እንደ ኃያል የውኃ ሞገድ የሚያስገመግም ድምጽ ለሚያሰሙ ሕዝቦች ወዮላቸው!


በመሸ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሽብር አለ! ከመንጋቱም በፊት አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፥ የበዘበዙንም ዕጣ ይህ ነው።


የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ የማይወገድ ድንኳን፥ ካስማውም ለዘለዓለም የማይነቀል፥ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።


እነሆ፥ አፈር ደልድለው የመሸጉ፥ ከተማይቱን ሊይዙአት ቀርበዋል፤ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፤ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዛፎችዋን ቁረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፤ በመካከልዋ ያለው ነገር ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።


ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቆርጣቸዋለህ፥ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios