Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሐጌ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምንም አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ‘ይህን ቤት በቀድሞ ክብሩ ሳለ ያየ ከመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ ምን መስሎ ይታያችኋል? ይህ በፊታችሁ ምንም እንዳይደለ የሚቈጠር አይደለምን?’

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “የዚህ ቤተ መቅደስ የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደ ነበረ ያየ ሰው በእናንተ መካከል አለን? ዛሬስ እንዴት ሆኖ ታዩታላችሁ? ይህ በእናንተ ዘንድ እንደሌለ የሚቈጠር አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de




ሐጌ 2:3
8 Referências Cruzadas  

ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።


ደግሞም ጌታን እያከበሩና እያመሰገኑ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ ዘመሩ። ሕዝቡ ሁሉ ጌታን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ፥ ይህም የጌታ ቤት ስለ ተመሠረተ ነው።


የመጀመሪያውን ቤት ያዩ ብዙ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የአባቶች አለቆችና ሽማግሌዎች ግን ይህ ቤት በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፥ ብዙ ሰዎችም በደስታ እልል ይሉ ነበር፤


የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ፥ ኢየሩሳሌምም የተተወች ሆናለች።


የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ።


የዚህ የኋለኛው ቤት ክብር ከፊተኛው ይልቅ ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios