Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፥ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፥ “ቃየን በገደለው በአቤል ምትክ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል” ስትል ሤት አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አዳምና ሔዋን ሲገናኙ እንደገና ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ እርስዋም “ቃየል በገደለው በአቤል ምትክ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ሰጠኝ” ስትል “ሤት” የሚል ስም አወጣችለት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፤ ወንድ ልጅንም ወለድች። ስሙንም፤ ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኚል ስትል ሴት አለችው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 4:25
7 Referências Cruzadas  

ቃየንም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ፥ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።


ሤትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሄኖስንም ወለደ፤


አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥


የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios