Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 24:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 “እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም፥ እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ ‘እስኪ አጠጪኝ’ አልኋት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 “በልቤ የምጸልየውን ጸሎት ገና ሳልጨርስ፣ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች፤ ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ ቀዳች። እኔም፣ ‘እባክሽ፤ ውሃ አጠጪኝ’ አልኋት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 የኅሊና ጸሎቴን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጒድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም ‘እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ’ አልኳት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 እኔም በልቤ ያሰ​ብ​ሁ​ትን ሳል​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እን​ስ​ራ​ዋን በት​ከ​ሻዋ ተሸ​ክማ ወጣች፥ ወደ ምን​ጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠ​ጪኝ” አል​ኋት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ እስኪ አጠጭኝ አልኍት።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 24:45
14 Referências Cruzadas  

እርሷም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ የምትለኝ፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ያዘጋጃት ሴት እርሷ ትሁን።’”


አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለአገልጋይህ ገልጸህለታል። ስለዚህ አገልጋይህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።


ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጋልህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ።


የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


“ጠይቁ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል።


ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው “በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና


እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios