Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ገላትያ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሁልጊዜ መልካም ለሆነ ነገር ሁሉ ብትቀኑ መልካም ነው፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ጋር ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዓላማው ጥሩ ከሆነ መትጋት ምንጊዜም መልካም ነው፤ ነገር ግን ይህ መትጋታችሁ እኔ ከእናንተ ጋር በምኖርበት ጊዜ ብቻ አይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መቅ​ና​ትስ ዘወ​ትር ለመ​ል​ካም ሥራ ልት​ቀኑ ይገ​ባል፤ ነገር ግን እኔ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባለ​ሁ​በት ጊዜ ብቻ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ገላትያ 4:18
13 Referências Cruzadas  

ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።


ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።


ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፥ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቁር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፥ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።


ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


ቀድሞ በሥጋ ድካም ወንጌልን እንደሰበክሁላችሁ ታውቃላችሁ፤


ይቀኑባችኋል፥ ለመልካም ግን አይደለም፤ ነገር ግን እናንተ በእነርሱ ላይ እንድትቀኑ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ።


አሁን ከእናንተ ጋር ተገኝቼ አነጋገሬን ብለውጥ በወደድሁ ነበር፥ በእናንተ ምክንያት ግራ ገብቶኛልና።


ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤


መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios