Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 40:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 አደባባዩንም ለካ፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ ወርዱም መቶ ክንድ አራት ማዕዘን ነበር፤ መሠዊያውም በቤቱ ፊት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ከዚያም አደባባዩን ለካው፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ መቶ ክንድ እኩል በእኩል ባለአራት ማእዘን ነበር። መሠዊያውም በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ያ ሰው የውስጠኛውን አደባባይ ሲለካ ርዝመቱ መቶ ክንድ ወርዱም መቶ ክንድ ሆነ፤ በቤተ መቅደሱ በፊት ለፊቱም አንድ መሠዊያ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም በአ​ራት ማዕ​ዘኑ ርዝ​መ​ቱን መቶ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቤቱ ፊት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 አደባባዩንም በአራት ማዕዘኑ ርዝመቱን መቶ ክንድ ወርዱንም መቶ ክንድ አድርጎ ለካ፥ መሠዊያውም በቤቱ ፊት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 40:47
5 Referências Cruzadas  

ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።


ከታችኛው በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ወርዱን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


በምሥራቁ በር እንዳለው ዓይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


በውስጠኛው አደባባይ በደቡብ በኩል በር ነበረ፤ በደቡብ በኩልም ከበር እስከ በር ድረስ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


ቤቱንም ለካው፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ ሆነ፥ የተለየው ስፍራ፥ ሕንጻውና ግንቡ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios