Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 40:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ እንደ ፊተኛው በር መጠናቸው እኩል ነበር፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንደ መጀመሪያው በር ሁሉ ይኸኛውም በየጐኑ ያሉት ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች፣ በየመካከሉ ወጣ ወጣ ያሉ ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው እኩል ነበር። ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ግራና ቀኝ ያሉት ሦስቱ የዘብ ማረፊያ ክፍሎችና የግድግዳ ዐምዶች እንዲሁም በስተመጨረሻ ያለው ክፍል በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ከታዩት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ልክ ነበራቸው፤ የቅጽር በሩ ጠቅላላ ርዝመት ኀምሳ ክንድ፥ ወርዱ ኻያ አምስት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የዕቃ ቤቶ​ቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግ​ንቡ አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ሳዩ ዘን​ባ​ባ​ዎ​ቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የዘበኛ ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፥ የግንቡ አዕማድና መዛነቢያዎቹም እንደ ፊተኛው በር ልክ ነበሩ፥ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 40:21
8 Referências Cruzadas  

ወደ ደቡብ መራኝ፥ እነሆ ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፤ የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ። ከሌሎቹም ጋር እኩል መጠን ነበራቸው።


ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።


መተላለፊያዎቹም ወደ ውጪው አደባባይ ይመለከቱ ነበር፤ በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር፤ መወጣጫውም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios