ሕዝቅኤል 39:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በምድርም የሚመላለሱት ሲያልፉ የሰው አጥንት ቢያዩ፥ ቀባሪዎች በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ በአጠገቡ ምልክት ያኖሩበታል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እነርሱም በምድሪቱ መካከል ሲሄዱ፣ ከእነርሱ አንዱ የሰው ዐፅም ባየ ቍጥር ምልክት ያደርግበታል፤ ይህም መቃብር ቈፋሪዎች በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በሀገሪቱም ውስጥ ሲዘዋወሩ የሰው ዐፅም በሚያገኙበት ጊዜ በጐኑ ምልክት አድርገውበት ያልፋሉ፤ መቃብር ቆፋሪዎችም መጥተው በሐሞን ጎግ ሸለቆ ይቀብሩታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በምድርም የሚዞሩት ያልፋሉ፤ የሰውንም አጥንት ቢያዩ፥ ቀባሪዎች በጎግ መቃብር ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ምልክት ያኖሩበታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በምድርም የሚዞሩት ያልፋሉ፥ የሰውንም አጥንት ቢያዩ፥ ቀባሪዎች በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ምልክት ያኖሩበታል። Ver Capítulo |