Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 39:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የእስራኤል ቤት ምድሪቱን ለማጽዳት ሰባት ወር ሙሉ ይቀብሩአቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ ‘ምድሪቱን ለማጽዳት፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ሙሉ ይቀብሯቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ያንን ሁሉ ሬሳ ቀብረው ምድሪቱን እንደገና ለማጽዳት ሰባት ወራት ይፈጅባቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ምድ​ር​ንም ያነ​ደዱ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰባት ወር መቃ​ብር እየ​ቈ​ፈሩ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ምድሩንም ያጸዱ ዘንድ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ይቀብሩአቸዋል፥

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 39:12
7 Referências Cruzadas  

በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።


ምድሪቱን ለማጽዳት በምድሪቱ ላይ ዘወትር የሚመላለሱና በምድር ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ ሰዎችን ይለያሉ፤ ከሰባቱ ወር በኋላ ፍለጋ ይጀምራሉ።


ደግሞም የከተማይቱ ስም ሐሞና ይባላል። ምድሪቱንም ያጸዳሉ።


“የሞተውን የማናቸውንም ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤


“ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ በዚያኑ ዕለት ቅበረው።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios