Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 37:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንደ ታዘዝሁት ትንቢት ተናገርሁ፤ ትንቢትንም ስናገር እነሆ የመንኰሻኰሽ ድምፅ ነበር፥ አጥንት ከአጥንቱ ጋር እየሆነ አጥንቶች አንድ ላይ ሆኑ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ እንደ ታዘዝሁት ትንቢት ተናገርሁ፤ ትንቢቱን በምናገርበትም ጊዜ የኵሽኵሽታ ድምፅ ተሰማ፤ ዐጥንቶቹም አንድ ላይ ሆኑ፤ ዐጥንት ከዐጥንት ጋራ ተጋጠመ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እኔም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ መናገርም እንደ ጀመርኩ የመንኰሻኰሽ ድምፅ ሰማሁ፤ አጥንቶቹም እርስ በርሳቸው እየተገጣጠሙ መያያዝ ጀመሩ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ስና​ገ​ርም ድምፅ ሆነ፤ እነ​ሆም መና​ወጥ ሆነ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም እየ​ራሱ በሆነ በሰ​ው​ነቱ ከአ​ጥ​ን​ቶች ጋር አንድ አደ​ረ​ጋ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 37:7
10 Referências Cruzadas  

ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ጌታ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ፥ ካህናትና ነቢያት ሕዝቡም ሁሉ፦ “ፈጽሞ ትሞታለህ።


እኔም እንደታዘዝኩት አደረግሁ፥ በቀንም ጓዙን እንደ ስደተኛ ጓዝ አወጣሁ፥ በምሽትም ጊዜ ግንቡን በእጄ ቦረቦርሁት፥ እያዩኝም በትከሻዬ ላይ ተሸክሜ በጨለማ አወጣሁት።


እኔም አየሁ፥ እነሆ ጅማትና ሥጋ ነበረባቸው፥ ቆዳም ከላይ እስከ ታች ሸፈናቸው፥ እስትንፋስ ግን በውስጣቸው አልነበረም።


ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፤ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።


ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተሰበረ፤ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉአቸው።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደሆነ ቁረጡ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios