Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 37:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አባቶቻችሁ በኖሩበት፣ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖራሉ። በዚያም እነርሱ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘላለም ይኖራሉ፤ ባሪያዬ ዳዊትም ለዘላለም ንጉሣቸው ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በኖ​ሩ​ባት፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆብ በሰ​ጠ​ኋት ምድር ይኖ​ራሉ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አለቃ ይሆ​ና​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አባቶቻችሁም በኖሩባት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፥ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፥ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 37:25
33 Referências Cruzadas  

ደግሞም፦ ‘እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፥ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘለዓለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።’” አለኝ።


ለስሜ ቤት የሚሠራ እርሱ ነው፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ።


ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘለዓለም የጸና ይሆናል።’ ”


ከእሴይ ግንድ ቁጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።


በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።


እነሆ፥ ለአሕዛብ ምስክር፥ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እንድከብር የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ።


እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።


እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል ጌታ፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱአታል፥ ይላል ጌታ።”


ነገር ግን ጌታ አምላካቸውንና የማስነሣላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።


የይሁዳና የከተሞችዋ ሕዝብ ሁሉ፥ ገበሬዎችና ከመንጋቸም ጋር የሚዞሩ በአንድነት በዚያ ይቀመጣሉ።


እኔን ለዘለዓለም በመፍራት ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።


ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል፥ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ በሰበሰብሁ ጊዜ፥ በአሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ ለባርያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ይቀመጣሉ።


እኔም ጌታ፥ አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ባርያዬ ዳዊትም በመካከላቸው አለቃ ይሆናል፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።


ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።


አንተም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ሕዝቦች መካከል እወስዳለሁ፥ ከየስፍራውም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ።


አገልጋዬ ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ በፍርዴ ይሄዳሉ፥ ትእዛዜን ይጠብቃሉ ይፈጽሟቸዋልም።


የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ።


መስፍኑ ብቻ በጌታ ፊት ምግብ ለመብላት ይቀመጥበታል፤ በበሩ መተላለፊያ መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።


ነገር ግን ይሁዳ ለዘለዓለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ይሆናል።


በምድራቸውም ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥” ይላል ጌታ አምላክህ።


የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በጌታ ሐሤት ያደርጋል።


ከተማዋም ሰዎች ይኖሩባታል፥ ከዚያም ወዲያ እርግማን አይኖርም። ኢየሩሳሌምም በሰላም ትኖራለች።


በኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲኖሩ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በታማኝነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


እንዲህ ሕዝቡ “እኛስ ክርስቶስ ለዘለዓለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።


ለእርሱም አብርሃም ከሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው፥፥ የስሙ ትርጓሜ በመጀመሪያ፥ የጽድቅ ንጉሥ ነው፤ ከዚያ ደግሞ፥ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው።


እነዚያ ከዚህ በፊት ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ እርሱ ግን ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና፤ “ጌታ ሐሳቡን አይቀይርም ‘አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ፤’ ብሎ ምሏል፥፥”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios