Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 31:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተዉት ሄደዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከምድር ሕዝቦች በጣም ጨካኞች የሆኑት ዛፉን ቈርጠው ይጥላሉ። ቀንበጦቹም በተራሮችና በሸለቆዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ቅርንጫፎቹ ተሰባብረው በወራጅ ውሃ ላይ ይጋደማሉ። በጥላው ሥር ተጠልለው የነበሩት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ትተውት ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች የሆኑ፥ ቈር​ጠው ጣሉት፤ በተ​ራ​ሮ​ችና በሸ​ለ​ቆ​ዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በም​ድር ፈሳ​ሾች ሁሉ ላይ ተሰ​ባ​በሩ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ከጥ​ላው ተመ​ል​ሰው ተዉት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሌላ አገር ሰዎች፥ የአሕዛብ ጨካኞች የሆኑ፥ ቈርጠው ጣሉት፥ በተራሮችና በሸለቆች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ከጥላው ተመልሰው ተውት።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 31:12
17 Referências Cruzadas  

ስለዚህ እነሆ ባዕዳንን፥ ጨካኞች መንግሥታትን አመጣብሃለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፥ ድምቀትህን ያረክሳሉ።


እርሱና ከሕዝቦች ሁሉ ርህራሄ የሌላቸው ሕዝቡ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፤ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በሬሳ ይሞላሉ።


ወንዞችን አደርቃለሁ፥ ምድሪቱን በክፉ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ፥ ምድሪቱንና ሞላዋን በባዕዳን እጅ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።


በሕዝቦች መካከል በጥላው የኖሩ ክንዱ ወደነበሩት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሲኦል ወረዱ።


በኃያላን ሰይፍ ብዙ ሕዝብህን እጥላለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ጨካኞች ናቸው፤ የግበጽንም ትዕቢት ያወድማሉ ብዛትዋም ሁሉ ይጠፋል።


የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥


ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህ፥ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ይወድቃሉ።


አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


በባዕድም እጅ ለዝርፊያ፥ በምድር ላሉ ክፉዎች እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እነርሱም ያረክሱአታል።


የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ ጠራርገው ይሄዳሉ፤ ኃይላቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ለመውረስ በምድር ሁሉ ላይ የሚሄዱትን፥ መራሮችና ችኩሎች ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios