Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 26:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሀብትሽን ይዘርፋሉ፥ ሸቀጣ ሸቀጥሽንም ይበዘብዛሉ፤ ቅጥርሽን ያፈርሳሉ፥ የተዋቡ ቤቶችሽን ያጠፋሉ፤ ድንጋይሽን፥ እንጨትሽንና አፈርሽን በውኆች መካከል ያስቀምጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሀብትሽን ይዘርፋሉ፤ ሸቀጥሽን ይበዘብዛሉ፤ ቅጥሮችሽን ያፈርሳሉ፤ የተዋቡ ቤቶችሽን ያወድማሉ፤ ድንጋይሽን፣ ዕንጨትሽንና የግንቦች ፍርስራሽ ወደ ባሕር ይጥላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሀብትሽ ይማረካል፤ የንግድ ዕቃሽ ይዘረፋል፤ ቅጥርሽ ይፈርሳል፤ የተዋቡ ቤቶችሽ ይፈራርሳሉ፤ ድንጋዮችሽ፥ ሳንቃዎችሽና ፍርስራሹ ወደ ባሕር ይጣላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ገን​ዘ​ብ​ሽን ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ መን​ጋ​ሽ​ንም ይዘ​ር​ፋሉ፤ አም​ባ​ሽ​ንም ይን​ዳሉ፤ የተ​ወ​ደዱ ቤቶ​ች​ሽ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ እን​ጨ​ቶ​ች​ሽ​ንና ድን​ጋ​ይ​ሽን፥ መሬ​ት​ሽ​ንም በባ​ሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥ​ሉ​ታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ብልጥግናሽንም ይማርካሉ፥ ሸቀጥሽንም ይበዘብዛሉ፥ ቅጥርሽንም ያፈርሳሉ፥ ተድላ የምታደርጊባቸውን ቤቶችሽን ያጠፋሉ፥ ድንጋይሽንና እንጨትሽን መሬትሽንም በባሕር ውስጥ ይጥላሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 26:12
19 Referências Cruzadas  

ለሕዝቅያስም እጅግ ብዙ ሀበትና ክብር ነበረው፤ ለብርና ለወርቅም፥ ለከበረው ዕንቁና ለሽቶው፥ ለጋሻውና ለከበረው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶች ሠራ።


ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።


እጁን በባሕር ላይ ዘረግቶ መንግሥታትንም አናውጧል፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ ጌታ አዟል።


አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?


ስለ ለሙ እርሻ፥ ስለፍሬያማውም ወይን ደረታችሁን ድቁ።


“ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።


ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሁሉ አፈረሰ።


በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ለሕዝቦችም ብዝበዛ ትሆናለች።


ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤ በባሕር ልብ ተገድለው በሞቱበት ሞት ትሞታለህ።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


እናንተም ድሀውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፥ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።


ነነዌ በዘመኗ ሁሉ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፤ እርሱም እየደረቀ ነው። “ቁሙ፥ ቁሙ” ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።


በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኳቸው። ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚዘዋወርባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios