Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 22:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም ጌታ መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ብር በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፣ እናንተም በከተማዪቱ ውስጥ ትቀልጣላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።’ ”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እነርሱም በእርስዋ ውስጥ ይቀልጣሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር የቊጣዬን ኀይል እንዳወረድኩባቸው ያውቃሉ።”

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 22:22
10 Referências Cruzadas  

እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፥ ሁሉም እያንዳንዱ የዓይኑን ርኩሰት አልጣለም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ፦ በግብጽ ምድር መካከል ቁጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


በአሕዛብም ፊት አንቺ ትረክሻለሽ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቂአለሽ።


እሰበስባችሁአለሁ፥ የመዓቴንም እሳት አነድባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


ስለዚህ ቁጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በምድር ላይ ባፈሰሱት ደምና በጣዖቶቻቸውም አርክሰዋታልና መዓቴን አፈሰስሁባቸው።


ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።


ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios