Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 20:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ደቡብ አዙር፤ በደቡብ ላይ ቃል ተናገር፤ በደቡብ አገር ደን ላይም ትንቢት ተንብይ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 “የሰው ልጅ ሆይ! ወደ ደቡብ ፊትህን አዙረህ በደቡብ ላይ ተናገር፤ በደቡብ በኩል ባለው ጫካ ላይም ትንቢት ተናገርበት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 “የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ቴማን አቅና፤ ወደ ዳሮ​ምም ተመ​ል​ከት፤ በና​ጌ​ብም ምድረ በዳ ዱር ንጉሥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፥

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 20:46
14 Referências Cruzadas  

ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፥ ንግግሬም በእነርሱ ላይ ተንጠባጠበ።


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል።


የጦር መሣሪያም የሚይዙትን አጥፊዎች በአንተ ላይ አዘጋጃለሁ፥ የተመረጡትንም የዝግባ ዛፎችህን ይቈርጣሉ፥ በእሳትም ውስጥ ይጥሉአቸዋል።


ስለዚህ ትንቢት ተናገርባቸው፥ የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አድርግ፥ ስለ መቅደሶችም ስበክ፤ በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተናገር


ጻድቁንና ክፉውን ከአንቺ ዘንድ ስለማስወግድ፥ ስለዚህ ሰይፌ ከደቡብ እስከ ሰሜን ባለ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።


ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ፊትህን ታዞራለህ፥ ክንድህን ዕራቁቱን አድርገህ ትንቢትን ትናገርባታለህ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርባቸው፤


“አሁን ደግሞ የጌታን ቃል ስማ፤ አንተ፦ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ አልህ፤


“አትስበኩ” ብለው ይሰብካሉ፤ “ስለ እነዚህ ነገሮች መስበክ የለባችሁም፤ ውርደት አይደርስብንም።”


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios