Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሕዝቅኤል 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሰው ጻድቅ ቢሆን፥ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “በቅንነትና በትክክል የሚሠራ፣ ጻድቅ ሰው ቢገኝ፣

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ሰው ጻድቅ፥ ፍትሓዊና ትክክለኛ ቢሆን፥

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥

Ver Capítulo Cópia de




ሕዝቅኤል 18:5
18 Referências Cruzadas  

ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


ጌታ ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል።


በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።


መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥


እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፥ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች የልጅም ነፍስ የእኔ ናት፥ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።


በተራሮች ላይ ባይበላ፥ ዐይኖቹን ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ፥ የባልንጀራውን ሚስት ባያረክስ፥ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፥


እኔም ኃጢአተኛውን ሰው፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥


እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ፥ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ ታውቃላችሁ።


ትእዛዛቱን ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።


ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፥ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios